የሚስዮን ስራ ደግሞም መስበክ; ወንጌል ተመልከቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በስራና በምሳሌ መካፈል። መድኃኒትንም የሚያወራ እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው, ኢሳ. ፶፪፥፯. እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ እፈልግማለሁ, ሕዝ. ፴፬፥፲፩. ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ, ማር. ፲፮፥፲፭ (ሞር. ፱፥፳፪). አዝመራውም አሁን እንደ ነጣ እርሻውን ተመልከቱ, ዮሐ. ፬፥፴፭. ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ, ሮሜ ፲፥፲፭. የእግዚአብሔርን ቃል በትጋት አስተምሯቸው, ያዕቆ. ፩፥፲፱. ጌታ ለሀገሮች ሁሉ ቃሉን እንዲያስተምሩ ሰጥቷል, አልማ ፳፱፥፰. የወንጌሌ ሙላት በደካሞች እና በተራ ሰዎች ይታወጅ, ት. እና ቃ. ፩፥፳፫. በሰዎች ልጆች መካከል ድንቅ ስራ ሊመጣ ነው, ት. እና ቃ. ፬፥፩. በቀኖቻችሁ ሁሉ ብታገለግሉ፣ እናም አንድም ነፍስም ቢሆን እንኳን ወደ እኔ ብታመጡ፣ ደስታችሁ እንዴት ታላቅ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፲፰፥፲፭. በእኔ የተመረጡት ድምጼን ይሰማሉ እና ልባቸውን አያደንድኑም, ት. እና ቃ. ፳፱፥፯. ወንጌሌን በመስበክ ሁለት በሁለት በመሆን ወደፊት ትሄዳላችሁ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፮. ድምፅ ከዚህ ቦታ ሁሉ ወደፊት መሄድ አለበት, ት. እና ቃ. ፶፰፥፷፬. አፎቻችሁን ከፍታችሁ ወንጌሌን ስበኩ, ት. እና ቃ. ፸፩፥፩. በሰጠኋችሁ ራዕዮች እና ትእዛዛት በኩል እውነቶችን አውጁ, ት. እና ቃ. ፸፭፥፬. የተጠነቀቀ ሰው ጎረቤቱን ማስጠንቀቁ አስፈላጊ ነው, ት. እና ቃ. ፹፰፥፹፩ (ት. እና ቃ. ፴፰፥፵–፵፩). ጌታ ወንጌልን ለሚሰብኩት ለቤተሰቦቻቸው እርዳታ ይሰጣል, ት. እና ቃ. ፻፲፰፥፫. የእግዚአብሔር አገልጋዮች ይሄዳሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፴፰. ታማኝ ሽማግሌዎችም ከዚህ ህይወት ሲሄዱ አገልግሎታቸውን ይቀጥላሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፶፯.