ቶማስ በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ በምድራዊ አገልግሎቱ ጊዜ በአዳኝ ከተመረጡት ቀዳሚ አስራ ሁለት ሐዋሪያት መካከል አንዱ (ማቴ. ፲፥፪–፫፤ ዮሐ. ፲፬፥፭፤ ፳፥፳፬–፳፱፤ ፳፩፥፪)። ምንም እንኳን የኢየሱስን ትንሳኤ አዳኝን በሰውነት እስከሚመለከት ድረስ ቢጠራጠርም፣ የግል ጸባይ ጥንካሬው ከጌታው ጋር መሰደድን እና ሞትን ለመቋቋም ፈቃደኛ እንዲሆን አደረገው (ዮሐ. ፲፩፥፲፮፤ ፳፥፲፱–፳፭)።