አንቲ-ኔፊ-ሌሂ ደግሞም አሞን፣ የሞዛያ ወንድ ልጅ; የሔለማን ልጆች; የሞዛያ ልጆች ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ በሞዛያ ወንድ ልጆች ለተቀየሩ ላማናውያን የተሰጠ ስም። ከተቀየሩ በኋላ፣ እነዚህ የአሞን ህዝቦች ተብለው የተጠሩ ህዝቦች በህይወቶቻቸው በሙሉ ታማኝ ነበሩ (አልማ ፳፫፥፬–፯፣ ፲፮–፲፯፤ ፳፯፥፳–፳፯)። አንቲ-ኔፊ-ሌሂዎች የሚል ስም ወሰዱ, አልማ ፳፫፥፲፮–፲፯፤ ፳፬፥፩. ደም ለማፍሰስ እምቢተኞች ሆኑ እናም የጦር መሳሪያዎቻቸውን ቀበሩ, አልማ ፳፬፥፮–፲፱. ልጆቻቸው ለጦርነት ተዘጋጁ እናም ሔለማንን እንደ መሪያቸው መረጡ, አልማ ፶፫፥፲፮–፲፱፤ ፶፮–፶፰። (ደግሞም እነዚህ ፳፻ ወጣት ጦረኞች ተብለው ይታወቃሉ።).