ገር፣ ገርነት ደግሞም ትሁት፣ ትሕትና; ትዕግስት; የተሰበረ ልብ ተመልከቱ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ጻድቅ፣ ትሁት፣ ለመማር ፈቃደኛ፣ እና በስቃይ ትእግስተኛ የሆነ። ትሁቶች የወንጌል ትምህርቶችን ለመከተል ፈቃደኞች ናቸው። ሙሴም እጅግ ትሑት ሰው ነበረ, ዘኁል. ፲፪፥፫. ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ, መዝ. ፴፯፥፲፩ (ማቴ. ፭፥፭; ፫ ኔፊ ፲፪፥፭; ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፯). እናንተ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ, ሶፎ. ፪፥፫ (፩ ጢሞ. ፮፥፲፩). ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና, ማቴ. ፲፩፥፳፱. የዋህነት የመንፈስ ፍሬ ነው, ገላ. ፭፥፳፪–፳፫. የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር ለማስተማርም የሚበቃ በትዕግሥትም የሚጸና የሚቃወሙትን በየዋህነት የሚያስተምር መሆን አለበት, ፪ ጢሞ. ፪፥፳፬–፳፭. በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለው ነው, ፩ ጴጥ. ፫፥፬. ተፈጥሮአዊው ሰውነትን ቀይር እናም የዋህ ይሁን, ሞዛያ ፫፥፲፱ (አልማ ፲፫፥፳፯–፳፰). እግዚአብሔር ሄላማንን ሰዎች የዋህ፣ እንዲሆኑ እንዲያስተምራቸው አዘዘ, አልማ ፴፯፥፴፫. የጌታ ፀጋ ለየዋሆች በቂ ነው, ኤተር ፲፪፥፳፮. የዋህ በመሆናችሁ በክርስቶስ እምነት አላችሁ, ሞሮኒ ፯፥፴፱. ማንም በልቡ የሚራራ እናም የዋህ ካልሆነ በጌታ ፊት ተቀባይነት አይኖረውም, ሞሮኒ ፯፥፵፬. የኃጢያት ስርየት የዋህነትን በመንፈስ ቅዱስ መጎብኘትን ያመጣል, ሞሮኒ ፰፥፳፮. በመንፈሴ በትህትና ተጓዝ, ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፫. ቤትህን በትህትና ግዛ, ት. እና ቃ. ፴፩፥፱. የክህነት ሀይል እና ተፅዕኖ ሊጠበቅ የሚቻለው በደግነት፣ እና በትሁትነት ነው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፵፩.