የጥናት እርዳታዎች
አስሩ ቃላት


አስሩ ቃላት

በነቢዩ ሙሴ በኩል የስነምግባር ጸባይን ለመቆጣጠር እግዚአብሔር የሰጣቸው አስር ቃላት።

በዕብራውያን ቋንቋ የእነዚህ ስም “አስር ቃላት” ነው። እነዚህም ቃል ኪዳን (ዘዳግ. ፱፥፱) ወይም ምስክር ተብለው ተጠርተዋል (ዘፀአ. ፳፭፥፳፩፴፪፥፲፭)። እግዚአብሔር አስሩን ቃላት ለሙሴ እና በእርሱም በኩል ለእስራኤል ሰጠ፣ በዘፀአ. ፲፱፥፱–፳፥፳፫፴፪፥፲፭–፲፱፴፬፥፩ ውስጥም ተገልጸዋል። ትእዛዛቱ የተቀረጹት በሁለት የድንጋይ ጽላት ላይ ነበር፣ እነዚህም በታቦት ውስጥ ተቀመጡ፤ ከዚህም ጀምሮ ታቦቱ የኪዳን ታቦት ተብለው ተጠርተዋል (ዘኁል. ፲፥፴፫)። ጌታ ከዘዳግ. ፮፥፬–፭ እና ከዘሌዋ. ፲፱፥፲፰ በመጥቀስ አስሩን ቃላት “በሁለቱ ትእዛዛት” አሳጥሮ በማጠቃለል ሰጥቷል (ማቴ. ፳፪፥፴፯–፴፱)።

አስሩ ቃላት በኋለኛው ቀን ራዕያት ውስጥ ደግመው ተሰጥተዋል (ጆ.ስ.ት.፣ ዘፀአ. ፴፬፥፩–፪፣ ፲፬ [ተጨማሪ]ሞዛያ ፲፪፥፴፪–፴፯፲፫፥፲፪–፳፬ት. እና ቃ. ፵፪፥፲፰–፳፰፶፱፥፭–፲፫)።