የኃጢያት ስርየት ደግሞም መጸጸት፣ ንስሀ መግባት; ኢየሱስ ክርስቶስ; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; ይቅርታ ማድረግ ተመልከቱ በንስሀ መግባት ላይ በመመካት ይቅርታ ማድረግ። የኃጢያት ስርየት ሊሆን የተቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ በኩል ነው። ሰው የኃጢያት ስርየትን የሚቀበለው በክርስቶስ እምነት ላለው፣ ለኃጢያቶቹ ከተጠመቀ፣ የጥምቀት እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለመቀበል እጆች የመጫን ስነስራአቶችን ከተቀበለ፣ እና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ካከበረ ነው። (እ.አ. ፩፥፫–፬)። ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች, ኢሳ. ፩፥፲፮–፲፰. ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ስርየት የሚፈስ ደሜ ይህ ነው, ማቴ. ፳፮፥፳፰ (ዕብ. ፱፥፳፪–፳፰; ት. እና ቃ. ፳፯፥፪). ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ ተጠመቁ, የሐዋ. ፪፥፴፰ (ሉቃ. ፫፥፫; ት. እና ቃ. ፻፯፥፳). በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላሉ, የሐዋ. ፲፥፵፫ (ሞዛያ ፫፥፲፫). ለኃጢአታቸው ስርየት መመልከት ያለባቸው ወደ ክርስቶስ ነው, ፪ ኔፊ ፳፭፥፳፮. የኃጢያቶችን ስርየት ለማግኘት፣ ደሀዎችን እና እርዳታ የሚፈልጉትን መንከባከብ ይገባናል, ሞዛያ ፬፥፲፩–፲፪፣ ፳፮. ማንኛውም ንስሃ የሚገቡ ለኃጢአታቸው ስርየት ይገባቸዋል, አልማ ፲፪፥፴፬. ትዕዛዙን መፈፀም የኃጢያት ስርየትን ያመጣል, ሞሮኒ ፰፥፳፭. የአሮናዊ ክህነት ለኃጢያት ስርየት በማጥለቅ የመጥመቅ ቁልፎች የያዘ ነው, ት. እና ቃ. ፲፫ (ት. እና ቃ. ፹፬፥፷፬፣ ፸፬; እ.አ. ፩፥፬). እኔ ጌታ ኃጢያቶቻቸውን ደግሜ አላስታውሳቸውም, ት. እና ቃ. ፶፰፥፵፪–፵፫ (ሕዝ. ፲፰፥፳፩–፳፪). ለኃጢያት ስርየት የውክልና ጥምቀትን ተምረው ነበር, ት. እና ቃ. ፻፴፰፥፴፫.