የጊዜዎች ምልክቶች ደግሞም ምልክት; የመጨረሻ ቀናት፣ የኋለኛው ቀናት; የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ተመልከቱ እግዚአብሔር ለህዝቦቹ በስራው አስፈላጊ ነገር እንደደረሰ ወይም በቅርብ እንደሚደርስ ለማሳየት የሚሰጠው ድርጊቶች ወይም አጋጣሚዎች። በኋለኛው ቀናት፣ ለአዳኝ ዳግም ምፅዓት ብዙ ምልክቶች ተተንብየዋል። እነዚህ ምልክቶች ታማኝ ሰዎች የእግዚአብሔርን አላማ እንዲያውቁ፣ እንዲጠነቀቁ፣ እና እንዲዘጋጁ ይፈቅድላቸዋል። የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል, ኢሳ. ፪፥፪–፫. ጌታ ምልክትን ያቆማልእናም እስራኤልን ይሰበስባል, ኢሳ. ፭፥፳፮ (፪ ኔፊ ፲፭፥፳፮–፴). ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፥ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም, ኢሳ. ፲፫፥፲ (ኢዩ. ፫፥፲፭; ት. እና ቃ. ፳፱፥፲፬). ሰዎች ሕጉን ተላልፈዋል፣ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋል, ኢሳ. ፳፬፥፭. የኔፋውያን ቃል ከአፈር ወጥቶ ይጮኻል, ኢሳ. ፳፱፥፬ (፪ ኔፊ ፳፯). እስራኤል በሀይል ትሰበሰባለች, ኢሳ. ፵፱፥፳፪–፳፫ (፩ ኔፊ ፳፩፥፳፪–፳፫; ፫ ኔፊ ፳–፳፩). እግዚአብሔር የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል, ዳን. ፪፥፵፬ (ት. እና ቃ. ፷፭፥፪). ጦርነት፣ ህልሞች፣ እና ራዕዮች ከዳግም መፅዓት በፊት ይታያሉ, ኢዩ. ፪. አሕዛብንም ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ ለሰልፍ ይሰበሰባለሉ, ዘካ. ፲፬፥፪ (ሕዝ. ፴፰–፴፱). እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል, ሚል. ፬፥፩ (፫ ኔፊ ፳፭፥፩; ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፷፬; ጆ.ስ.—ታ. ፩፥፴፯). ከዳግም ምፅዓት በፊት ታላቅ አደጋዎች ይመጣሉ, ማቴ. ፳፬ (ጆ.ስ.—ማቴ. ፩). ጳውሎስ ክህደትን እና የመጨረሻ ቀናት አሰቃቂ ጊዜዎችን ገለጸ, ፪ ጢሞ. ፫–፬. ሁለት ነቢያት ይገደላሉ እናም በኢየሩሳሌም ከሞት ይነሳሉ, ራዕ. ፲፩ (ት. እና ቃ. ፸፯፥፲፭). ወንጌል በመጨረሻው ቀናት በመላእክት አገልግሎት በዳግም ይመለሳሉ, ራዕ. ፲፬፥፮–፯ (ት. እና ቃ. ፲፫; ፳፯; ፻፲፥፲፩–፲፮; ፻፳፰፥፰–፳፬). ባቢሎስ ትመሰረታለች እናም ትወድቃለች, ራዕ. ፲፯–፲፰. እስራኤል በሀይል ትሰበሰባለች, ፩ ኔፊ ፳፩፥፲፫–፳፮ (ኢሳ. ፵፱፥፲፫–፳፮; ፫ ኔፊ ፳–፳፩). እናም እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች፣ ህዝቤን የእስራኤልን ቤት፣ ለረጅም ጊዜ ከተበተኑበት የምሰበስበት፣ እናም በድጋሚም ፅዮንንም በመካከላቸው የምመሰርትበት የሚፈፀሙበትን ጊዜ ታውቁ ዘንድ ምልክትን እሰጣችኋለሁ, ፫ ኔፊ ፳፩፥፩. ጊዜውን ታውቁ ዘንድ ይህ ምልክት ነው, ሞር. ፰. ላማናውያንም ያብባሉ, ት. እና ቃ. ፵፱፥፳፬–፳፭. ኃጢያተኞች ኃጢያተኞችን ይገድላሉ, ት. እና ቃ. ፷፫፥፴፪–፴፭ (ራዕ. ፱). በሁሉም ህዝቦች ላይ ጦርነት ይፈሳል, ት. እና ቃ. ፹፯፥፪. ምልክቶች የንጥረ ነገር ብጥበጣ፣ እና መላእክቶች ለጌታ መምጣት መንገድን ያዘጋጃሉ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፹፮–፺፬. ጭለማ ምድርን ይሸፍናል, ት. እና ቃ. ፻፲፪፥፳፫–፳፬. ጌታ ቅዱሳንን ለዳግም ምፅዓት እንዲዘጋጁ አዘዘ, ት. እና ቃ. ፻፴፫.