ለሙታን ደህንነት
ይህም የሚያድኑ የወንጌል ስነስርዓዮችን ሳይቀበሉ ለሞቱት እነዚህን ስነስርዓቶች ብቁ በሆኑ ህያው የቤተክርስቲያን አባላት ለእነርሱ በቤተመቅደስ ውስጥ የማከናወን እድል ነው። ሙታን ወንጌልን በመንፈስ አለም ውስጥ ተምረዋል እናም በስጋዊነት የተከናወነላቸውን ስነስርዓቶች መቀበልን ይችላሉ።
ታማኝ የቤተክርስቲያኗ አባላት የሚያድኑት ስነስርዓቶች ለእነርሱ ይከአንወንላቸው ዘንድ የቅድመ አባቶቻቸውን ስም እና የልደት ቀን ለማወቅ የቤተሰብን ታሪክ ይፈትሻሉ እናም ያዘጋጃሉ።