የጥናት እርዳታዎች
ሔኖክ


ሔኖክ

የፅዮን ከተማ ህዝቦችን የመራ ነቢይ። አገልግሎቱ በብሉይ ኪዳን እና በየታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ ተወያይተዋል። ከአዳም በኋላ ሰባተኛው የአባቶችም አለቃ ነበር። የያሬድ አባት እና የማቱሳላ አባት ነበር (ዘፍጥ. ፭፥፲፰–፳፬ሉቃ. ፫፥፴፯)።

ሔኖክ ታላቅ ሰው ነበር እና የመፅሐፍ ቅዱስ አጭር ታሪክ ከሚገልጸው በላይ ታላቅ የሆነ አገልግሎት ነበረው። መፅሐፍ ቅዱስ እንደተቀየረ ይጠቅሳል (ዕብ. ፲፩፥፭) ነገር ግን ስለአገልግሎቱ ምንም መግለጫ አይሰጥም። ይሁዳ ፩፥፲፬ የተነበየውን ይጠቅሳል። የኋለኛው ቀን ራዕይ ስለሔኖክ፣ በልዩም ስለስበካው፣ ፅዮን ተብላ ስለተጠራችው ከተማው፣ ስለራዕዩ፣ እና ስለትንቢቶቹ በተጨማሪ ይገልጻል (ት. እና ቃ. ፻፯፥፵፰–፶፯ሙሴ ፮–፯)። ፅዮን በእዚያ በሚኖሩት ጽድቅ ምክንያት ወደሰማይ ተወስዳለች (ሙሴ ፯፥፷፱)።