መከር አንዳንድ ጊዜ ቅዱስ መጻህፍቶች መከር ሰዎችን በምድር ላይ የእግዚአብሔር መንግስት ወደሆነችው ወደ ቤተክርስቲያኗ እንደ ማምጣት፣ ወይም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት አይነት ፍርድ ጊዜ እንደ ማምጣት ምሳሌአዊነት ይጠቀሙበታል። መከሩ አልፎአል፥ በጋው ሄዶአል፥ እኛም አልዳንም, ኤር. ፰፥፳ (ት. እና ቃ. ፶፮፥፲፮). መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው, ማቴ. ፱፥፴፯. መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው, ማቴ. ፲፫፥፴፱. ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል, ገላ. ፮፥፯–፱ (ት. እና ቃ. ፮፥፴፫). የእርሻው ስፍራ ነጭ ሆኖ ለመከር ዝግጁ ነው, ት. እና ቃ. ፬፥፬. መከሩ ያልፋል፣ እና መንፈሳችሁም አይድኑም, ት. እና ቃ. ፵፭፥፪. የመከር ጊዜ መጥቷል፣ እና ቃሌም መፈጸም አለበት, ት. እና ቃ. ፻፩፥፷፬.