የጥናት እርዳታዎች
ህግ


ህግ

በሰማይ ውስጥ እናም በምድር ውስጥ ሁሉም በረከቶች እና ቅጣቶች የሚመረኮዙባቸው የእግዚአብሔር ትእዛዛት ወይም ደንብ። የእግዚአብሔርን ህግ የሚያከብሩ በተስፋ ቃል የተሰጡትን በረከቶች ይቀበላሉ። ነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ ሰዎች ለምድር ህግጋት ታዛዥ መሆን፣ ማክበር፣ እና መደገፍ እንዳለባቸው አስተምሯል (እ.አ. ፩፥፲፪)።

የሙሴ ህግ ወንዶችን እና ሴቶችን ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ የመዘጋጃ ህግ ነበር። ይህም የመገደቢያ፣ መደረግ የሚገባውን ማዘዣ፣ እና የስነስርዓቶች ህግ ነበር። ዛሬ የሙሴን ህግ ያሟላው የክርስቶስ ህግ የወንጌሉ ሙላት ወይም “ነጻ የሚያወጣው ፍጹሙ ሕግ” ነው (ያዕ. ፩፥፳፭)።