ቅዱሳን ደግሞም ክርስቲያኖች; የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን; የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተመልከቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ታማኝ አባላት። ከእርሱ ጋር ለመሥዋዕት ኪዳን የቆሙትን ቅዱሳኑን ሰብስቡለት, መዝ. ፶፥፭. ሳዖል በኢየሩሳሌም ቅዱሳን ላይ ብዙ ክፉ ነገሮች አደረገ, የሐዋ. ፱፥፩–፳፩. ጴጥሮስም በልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ, የሐዋ. ፱፥፴፪. ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን, ሮሜ ፩፥፯. ከቅዱሳን ጋር ባላገሮች ናችሁ, ኤፌ. ፪፥፲፱–፳፩. የእግዚአብሔር ቅዱሳን የሆኑት የበጉ ቤተክርስቲያን ተመለከትኩ, ፩ ኔፊ ፲፬፥፲፪. ተፈጥሮአዊው ሰው በጌታ በክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ አማካኝነት ቅዱስ ካልሆነ ለእግዚአብሔር ጠላት ነበረ, ሞዛያ ፫፥፲፱. እኔ ጌታ ምድርን ለቅዱሳኖች ጥቅም ባርኬዋለሁ, ት. እና ቃ. ፷፩፥፲፯. ሰይጣን ከእግዚአብሔር ቅዱሳን ጋር ይዋጋል, ት. እና ቃ. ፸፮፥፳፰–፳፱. ቅዱሳንን ለሚመጣው የፍርድ ሰአት ለማዘጋጀት በትጋት ስሩ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፹፬–፹፭. እቃዎቻቸውን በቅዱሳን እንደሚገባው ለደሀዎችና በመካከላቸው ለሚሰቃዩት ያካፍሉ, ት. እና ቃ. ፻፭፥፫. የበላይ ሀላፊዎችን ለአገልግሎቱ ስራዎችና ለቅዱሳኔ ፍጹምነት ሰጥቻችኋለሁ, ት. እና ቃ. ፻፳፬፥፻፵፫ (ኤፌ. ፬፥፲፪).