የጥናት እርዳታዎች
ኦሪት ዘፍጥረት


ኦሪት ዘፍጥረት

ኦሪት ዘፍጥረት የብሉይ ኪዳን የመጀመሪያ መፅሐፍ ነው እናም በነቢዩ ሙሴ የተጻፈ ነበር። ስለ ምድር መፈጠር፣ እንስሳትና ሰው በምድር ላይ መደረግ፣ የአዳምና የሔዋን ውድቀት፣ ለአዳም ስለተገለጸው የጎሳዎችና የዘሮች መጀመሪያ፣ የተለያዩ ቋንቋዎች በባቢሎን የተጀመሩበት፣ እናም ወደ እስራኤል ቤት መመስረት የመራው የአብርሐም ቤተሰብ መጀመሪያ አይነት ብዙ የመጀመሪያዎች ታሪክ ይሰጣል። የጆሴፍ የእስራኤል አዳኝ ሀላፊነት በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ አፅንኦት ተሰጥቶታል።

የኋለኛው ቀን ራዕይ የኦሪት ዘፍጥረት ታሪኮችን ያረጋግጣል እናም ይገልጻል (፩ ኔፊ ፭ኤተር ፩ሙሴ ፩–፰አብር. ፩–፭)።

በኦሪት ዘፍጠርት ውስጥ፣ ምዕራፍ ፩–፬ የአለም መፈጠርን እና የአዳም ቤተሰብ እድገት ታሪክን ይነግራሉ። ምዕራፍ ፭–፲ የኖህን ታሪክ ይመዘግባሉ። ምዕራፍ ፲፩–፳ እስከ ይስሐቅ ድረስ ስለ አብርሐምና ቤተሰቡ ይነግራሉ። ምዕራፍ ፳፩–፴፭ የይስሐቅን ቤተሰብ ይከተላሉ። ምዕራፍ ፴፮ ስለ ዔሳውና ቤተሰቡ ይናገራል ምዕራፍ ፴፯–፶ ስለ ያዕቆብ ቤተሰብና ወደ ግብፅ ስለተሸጠው ዮሴፍ እና የእስራኤል ቤትን ለማዳን ስላለው ሀላፊነት ታሪክ ይናገራሉ።