መግደላዊት ማርያም የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ደቀ መዝሙር የሆነች የአዲስ ኪዳን ሴት። መግደላዊ ማርያም የመጣችበትን ቦታ፣ መጌዶልን፣ የሚጠቁም ነበረ። ይህም የተገኘው በገሊላ ባህር በምዕራብ ባህር ዳር ነበር። በመስቀሉ አጠገብ ነበረች, ማቴ. ፳፯፥፶፮ (ማር. ፲፭፥፵; ዮሐ. ፲፱፥፳፭). ክርስቶስ በሚቀበርበትም ጊዜ ነበረች, ማቴ. ፳፯፥፷፩ (ማር. ፲፭፥፵፯). ከሞት በተነሳበት ጠዋትም በመቃብሩ አጠገብ ነበረች, ማቴ. ፳፰፥፩ (ማር. ፲፮፥፩; ሉቃ. ፳፬፥፲; ዮሐ. ፳፥፩፣ ፲፩). ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በእርሷ ነበር, ማር. ፲፮፥፱ (ዮሐ. ፳፥፲፬–፲፰). ሰባት አጋንንት ወጡላት, ሉቃ. ፰፥፪.