የነሀስ ሰሌዳዎች
ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ ፮፻ ም.ዓ. ድረስ የብዙ ነቢያትን ፅሁፎች የያዘ በአይሁዶች የተጠበቀ መዝገብ (፩ ኔፊ ፭፥፲–፲፮)። ይህ መዝገብ በኢየሩሳሌም ውስጥ ከአይሁዶች ሽማግሌዎች መካከል አንዱ በሆነው በላባን ይጠበቅ ነበር። ሌሂ እና ቤተሰቡ በምድረበዳ ውስጥ እያሉ፣ ሌሂ ወንድ ልጆቹን ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ይህን መዝገብ እንዲያገኙ ላካቸው (፩ ኔፊ ፫–፬)። (ለተጨማሪ መረጃ፣ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኘውን “ስለመፅሐፈ ሞርሞን አጭር መግለጫ” ተመልከቱ።)