የከሞራ ኮረብታ
በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ፣ በምእራብ ኒው ዮርክ ውስጥ የሚገኝ ትንሽ ኮረብታ። በዚህም ሞሮኒ የሚባል የጥንት ነቢይ አንዳንዱን የኔፋውያን እና የያሬዳውያን መዝገቦችን የያዘውን የወርቅ ሰሌዳዎች የደበቀበት ነው። በ፲፰፳፯ (እ.አ.አ.) ጆሴፍ ስሚዝ እነዚህን ሰሌዳዎች እንዲያገኝና ከእነዚህ ክፍሎችም እንድተረጉም ወደዚህ ኮረብታ ከሞት በተነሳው ሞሮኒ ተመራ። ይህም ትርጉም መፅሐፈ ሞርሞን ነው።