የጥናት እርዳታዎች
ዲያብሎስ


ዲያብሎስ

ሰይጣን ዲያብሎስ ጽድቅንና የእግዚአብሔርን ፍላጎት ለሚፈልጉት ጠላት ነው። እርሱም የእግዚአብሔር የመንፈስ ልጅ እናም በአንድ ጊዜም በእግዚአብሔር ፊት ስልጣን የነበረው መልአክ ነበር። ነገር ግን፣ በቅድመ ምድራዊ ህይወት አመጸና የአብን አንድ ሶስተኛ የመንፈስ ልጆች ከእርሱ ጋር እንዲያምጹ አሳመናቸው (ኢሳ. ፲፬፥፲፪፪ ኔፊ ፪፥፲፯) (ት. እና ቃ. ፳፱፥፴፮ሙሴ ፬፥፩–፬አብር. ፫፥፳፯–፳፰)። ከሰማይ ተወረወሩ፣ ስጋዊ ሰውነት የማግኘትና ምድራዊ ህይወት ለማግኘት እድል አልተሰጣቸውም፣ እናም ለዘለአለምም ተኮነኑ። ዲያብሎስ ከሰማይ ከተወረወረ ጊዜ በኋላ፣ የሰውን ዘር ሁሉ እንደ እርሱ መከረኛ እንዲሆኑ ሁሉንም ወንዶችና ሴቶች ለማታለል እና ከእግዚአብሔር ስራ ውጪ መርቶ ለመውሰድ በየጊዜው ሞክሯል(ራዕ. ፲፪፥፱፪ ኔፊ ፪፥፳፯፱፥፰–፱)።

የዲያብሎስ ቤተክርስቲያን

በምድር ውስጥ ንጹህንና ፍጹም የሆነውን ወንጌል የሚለውጡና ከእግዚአብሔር ጥቦ ጋር የሚዋጉ ክፉ እና አለማዊ የሆኑ ድርጅቶች።