የእግዚአብሔር ሚስጥሮች የእግዚአብሔር ሚስጥሮች በራዕይ ብቻ የሚታወቁ መንፈሳዊ እውነቶች ናቸው። እግዚአብሔር ሚስጥሮቹን ለወንጌሉ ታዛዥ ለሚሆኑት ይገልጻል። የእግዚአብሔር አንዳንድ ሚስጥሮች ገና አልተገለጹም። ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል, ማቴ. ፲፫፥፲፩. ምሥጢርንም ሁሉ ባውቅ፥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ, ፩ ቆሮ. ፲፫፥፪. ኔፊ የእግዚአብሔርን ሚስጥር ታላቅ ዕውቀት ነበረው, ፩ ኔፊ ፩፥፩. ለብዙዎች የእግዚአብሔርን ሚስጥር እንዲያውቁ ተሰጥቷቸዋል, አልማ ፲፪፥፱. ለእንደእነዚህ ዓይነቶቹ የእግዚአብሔርን ሚስጥር እንዲያውቁ ይሰጣቸዋል, አልማ ፳፮፥፳፪. እነዚህ ሚስጥሮች ሙሉ በሙሉ ለእኔ አልታወቁኝም, አልማ ፴፯፥፲፩. እግዚአብሔር እራሱ ካልሆነ በቀር ማንም የማያውቃቸው ብዙ በአምላክ የተደበቁ ሚስጥሮች አሉ, አልማ ፵፥፫. የአምላክነት ሚስጥር እንዴት ታላቅ ነው, ት. እና ቃ. ፲፱፥፲. ከጠየቃችሁ፣ ራዕይ ትቀበላላችሁ፣ እናም የመንግስት ሚስጥራትን ታውቃላችሁ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፷፩፣ ፷፭ (፩ ቆሮ. ፪፥፯፣ ፲፩–፲፬). ትእዛዛቴን ለሚጠብቀው የመንግስቴን ሚስጥሮች እሰጠዋለሁ, ት. እና ቃ. ፷፫፥፳፫. ለእነርሱም ሁሉንም ሚስጥሮች እገልጻለሁ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፯. ታላቅ የክህነት የሚስጥር ቁልፎችን ይዟል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፱. ጌታ በሚመጣበት ጊዜ ማንም ሰው የማያውቃቸውን የተደበቁ ነገሮችን ይገልጻል, ት. እና ቃ. ፻፩፥፴፪–፴፫. የመልከ ጼዴቅ ክህነት የሰማይ መንግስትን ሚስጥሮች ለመቀበል ልዩ መብት ይኑረው, ት. እና ቃ. ፻፯፥፲፱.