ቆርያንቱመር ደግሞም ያሬዳውያን ተመልከቱ በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ፣ የያሬዳውያን ንጉስ እና የያሬዳውያን ህዝብ በመጨረሻ የተረፈ። በዛራሔምላ ህዝብ ተገኘ, ኦምኒ ፩፥፳፩. በምድሩ ላይ ሁሉ ንጉስ ነበር, ኤተር ፲፪፥፩–፪. በሻረድ ተያዘ እናም በልጆቹ ነጻነትን አገኘ, ኤተር ፲፫፥፳፫–፳፬. ከተለያዩ ጠላቶች ጋር ተዋጋ, ኤተር ፲፫፥፳፰–፲፬፥፴፩. ንስሀ ገባ, ኤተር ፲፭፥፫. የመጨረሻውን ጦርነት ከሺዝ ጋር ተዋጋ, ኤተር ፲፭፥፲፭–፴፪.