ማምለክ ደግሞም እግዚአብሔር፣ አምላክ ተመልከቱ ፍቅር፣ አምልኮ፣ አገልግሎት፣ እና ለእግዚአብሔር ታማኝነት (ት. እና ቃ. ፳፥፲፱)። አምልኮ በተጨማሪም ጸሎት፣ ጾም፣ የቤተክርስቲያን አገልግሎት፣ በወንጌል ስነስርዓቶች መሳተፍ፣ እና ለእግዚአብሔር ያለን ታማኝነት እና ፍቅር የማሳየት ሌሎች ልብዶች ነው። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ, ዘፀአ. ፳፥፫ (ዘፀአ. ፴፪፥፩–፰፣ ፲፱–፴፭; መዝ. ፹፩፥፱). ለአብ በመንፈስና በእውነት ስገዱ, ዮሐ. ፬፥፳፫. ሰማይንና ምድርንም ለሠራው ስገዱለት, ራዕ. ፲፬፥፯ (ት. እና ቃ. ፻፴፫፥፴፰–፴፱). እርሱን በሙሉ ኃይላችሁ፣ አእምሮአችሁ እና ጉልበታችሁ ማምለክ አለባችሁ, ፪ ኔፊ ፳፭፥፳፱. በክርስቶስ አምነዋል እናም አብንም በስሙ አምልከዋል, ያዕቆ. ፬፥፭. ሰዎች በሁሉም ቦታዎች መጸለይ እና ማምለክ እንደሚገባቸው ዜኖስ አስተማረ, አልማ ፴፫፥፫–፲፩. ላችሁበት ስፍራ ሁሉ በመንፈስና በእውነት እግዚአብሔርን አምልኩ, አልማ ፴፬፥፴፰. ህዝቡም በኢየሱስ እግር ስር ወደቁ፣ እናም አመለኩት, ፫ ኔፊ ፲፩፥፲፯. ሁሉም ሰው ንስሀ መግባትና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማመን፣ እናም አብን በእርሱ ስም ማምለክ አለባቸው, ት. እና ቃ. ፳፥፳፱. እነዚህን አባባል የምሰጣችሁ እንድትረዱ እና እንዴት እንደምታመልኩ እንድታውቁ፣ እና ምን እንደምታመልኩ እንድታውቁ ነው, ት. እና ቃ. ፺፫፥፲፱. ይህን አንድ እግዚአብሔር አመልካለሁ, ሙሴ ፩፥፲፪–፳. ሁሉን የሚችለው እግዚአብሔርን የማምለክ መብት እንዳለን እናረጋግጣለን, እ.አ. ፩፥፲፩.