የጥናት እርዳታዎች
መፅሐፈ መክብብ


መፅሐፈ መክብብ

በብሉይ ኪዳን ውስጥ የህይወት ጥልቅ ፈተናዎች ላይ ማሰላሰሊያን የያዘ መፅሐፍ።

የመፅሐፉ ጸሀፊ፣ ሰባኪው፣ አብዛኛውን የጻፈው የወንጌል እውቀት በሌላቸው አስተሳሰብ በኩል ነው። የጻፈውም በአለም ህዝቦች ስሜቶች መሰረት ነው—ይህም ማለት፣ “በጸሀይ ስር” ለነበሩት (መክ. ፩፥፱)። ከመፅሐፉ አብዛኛው መጥፎ ነገሮችን የሚጠቁምና ክፉ አሳቢዎች ያሉበት ይመስላል (መክ. ፱፥፭፣ ፲)። ጌታ ህይወትን እንደዚህ እንድናስብበት አይፈልግም ነገር ግን ሰባኪዎች በምድር ላይ ላሉ ላልተብራሩ ሰዎች ነገሮች እንደሚታዩአቸው የተመለከቱበት ነው። በመፅሐፉ ውስጥ ከሁሉም በላይ መንፈሳዊ ክፍሎች የሚገኙት በምዕራፍ ፲፩ እና ፲፪ ውስጥ ነው፣ በዚህም ጸሀፊው እስከ መጨረሻ ድረስ ዋጋ የሚኖረው ብቸኛ ነገር ቢኖር ለእግዚአብሔር ትእዛዛት ታዛዥነት ነው ብሎ ደምድሟል።