የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ደግሞም ቅዱሳን; የኋለኛው ቀን ቅዱሳን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን; የቤተክርስቲያን ስም; የእውነተኛ ቤተክርስቲያን ምልክቶች; የእግዚአብሔር መንግስት ወይም መንግስተ ሰማያት; የወንጌል ዳግም መመለስ ተመልከቱ በጥምቀት እና በመረጋገጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በራሳቸው ላይ የወሰዱ የሚያምኑ ሰዎች ድርጅት። እውነተኛ ቤተክርስቲያን ለመሆን ይህም የጌታ ቤተክርስቲያን መሆን አለበት፤ የእርሱ ስልጣን፣ ትምህርቶች፣ ህግጋት፣ ስነስርዓቶች፣ እና ስም ሊኖረው ይገባዋል፤ እንዲሁም እርሱ በመደባቸው ወኪሎቹ በኩል እርሱ ይህን መግዛት አለበት። ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በቤተክርስቲያኗ ላይ ጨምሯል, የሐዋ. ፪፥፵፯. ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን, ሮሜ ፲፪፥፭. እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናል, ፩ ቆሮ. ፲፪፥፲፫. ቤክርስቲያኗ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ተጸንሳለች, ኤፌ. ፪፥፲፱–፳. ሐዋሪያትና ነቢያት ለቤተክርስቲያኗ አስፈላጊ ናቸው, ኤፌ. ፬፥፲፩–፲፮. ክርስቶስ የቤተክርስቲያን ራስ ነው, ኤፌ. ፭፥፳፫. ብዙ ቤተክርስቲያኖች ቢኖሩም ሁሉም አንድ ቤተክርስቲያን ነበሩ, ሞዛያ ፳፭፥፲፱–፳፪. ቤተክርስቲያኗ ጸዳች እናም በስርዓት ተስተካከለች, አልማ ፮፥፩–፮. የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በስሙ መጠራት አለባት, ፫ ኔፊ ፳፯፥፰. ለመፆምና ለመፀለይ እንዲሁም ለመነጋገር ሁልጊዜ በቤተክርስቲያን ተገናኙ, ሞሮኒ ፮፥፭. ይህች እውነተኛና ህያው ቤተክርስቲያን ናት, ት. እና ቃ. ፩፥፴. የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በእነዚህ በመጨረሻው ቀናት ተነሳች, ት. እና ቃ. ፳፥፩. ጌታ ቤተክርስቲያኑን እንዲገነቡ አገልጋዮቹን ጠራ, ት. እና ቃ. ፴፱፥፲፫. እንደዚህም ቤተክርስቲያኔ በመጨረሻው ቀናት ትጠራለች, ት. እና ቃ. ፻፲፭፥፬.