ሀይል ደግሞም ስልጣን; ክህነት ተመልከቱ አንድ ነገርን የማድረግ ችሎታ። በአንድ ሰው ወይም በአንድ ነገር ላይ ሀይል መኖር ያን ሰው ወይም ነገር ለመቆጣጠር ወይም ለማዘዝ ችሎታ መኖር ነው። በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ሀይል ከእግዚአብሔር ሀይል ወይም ከሰማይ ሀይል ጋር የተያያዘ ነው። ይህም ብዙ ጊዜ ለእግዚአብሔር ስራ ፈቃድ ወይም መብት ከሆነው ከክህነት ስልጣን ጋር የተያያዘ ነው። ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ, ዘፀአ. ፱፥፲፮. እግዚአብሔር ኃይልን የሚያስታጥቀኝ ነው, ፪ ሳሙ. ፳፪፥፴፫. በጎ ነገርን ማድረግ አትከልክል፥ ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን, ምሳ. ፫፥፳፯. በእግዚአብሔር መንፈስ ብርታትንም ተሞልቻለሁ, ሚክ. ፫፥፰. ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ, ማቴ. ፳፰፥፲፰. ቃሉ በሥልጣን ነበርና በትምህርቱ ተገረሙ, ሉቃ. ፬፥፴፪. እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ, ሉቃ. ፳፬፥፵፱. ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው, ዮሐ. ፩፥፲፪ (ት. እና ቃ. ፲፩፥፴). መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ, የሐዋ. ፩፥፰. ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለም, ሮሜ ፲፫፥፩. ለመዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ተጠብቃችኋል, ፩ ጴጥ. ፩፥፫–፭. በእግዚአብሔር ኃይል ተሞልቻለሁ, ፩ ኔፊ ፲፯፥፵፰. ለእኔ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተገልጾልኛል, ያዕቆ. ፯፥፲፪. ሰው ከእግዚአብሔር የተሰጠ ታላቅ ኃይል ሊኖረው ይችላል, ሞዛያ ፰፥፲፮. በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን አስተማሩ, አልማ ፲፯፥፪–፫. ኔፊ በሃይል እንዲሁም በታላቅ ሥልጣን አገለገለ, ፫ ኔፊ ፯፥፲፭–፳ (፫ ኔፊ ፲፩፥፲፱–፳፪). ሰው ብዙ ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት ሃይል ቢኖረውም፣ ነገር ግን በራሱ ጥንካሬ ቢታበይ፣ እርሱም መውደቅ አለብት, ት. እና ቃ. ፫፥፬. መልካም የማድረግ ሀይል ሁሉም ሰው አለው, ት. እና ቃ. ፶፰፥፳፯–፳፰. በመልከ ጼዴቅ ክህነት ስነስርዓቶች የአምላክነት ሀይል ይገለጻል, ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፱–፳፪. የክህነት ሀይል ከሰማይ ሀይሎች ጋር ሳይለያዩ የተያያዙ ናቸው, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፴፬–፵፮. በእጄም እመራሀለሁ፣ እናም ሀይሌም አንተ ላይ ያርፋል, አብር. ፩፥፲፰.