ኤርምያስ
በካህናት ቤተሰብ ውስጥ የተወለደ እና በይሁዳ ውስጥ ከ፮፻፳፮ እስከ ፭፻፹፮ ም.ዓ. ድረስ የተነበየ የብሉይ ኪዳን ነቢይ። በታላቆቹ ነቢያት፣ በሌሂ፣ በህዝቅኤል፣ በሆሴዕ፣ እና በዳንኤል ዘመን አቅራቢያ የኖረ ነበር።
በቅድመ ምድር ህይወት ነቢይ እንዲሆን ተሹሞ ነበር (ኤር. ፩፥፬–፭)። ወደ አርባ አመታት በሆኑት የነቢይነት አገልግሎት ጊዜዎቹ፣ ጣዖት ማምለክን እና ምግባረ መጥፎ የሆኑትን ከአይሁዳ ህዝቦች መካከል ስለማስወገድ አስተማረ (ኤር. ፫፥፩–፭፤ ፯፥፰–፲)። በየጊዜውም ተቃራኒ መሆንን እና ስድቦችን መፅናት ነበረበት (ኤር. ፳፥፪፤ ፴፮፥፲፰–፲፱፤ ፴፰፥፬)። ከኢየሩሳሌም ውድቀት በኋላ፣ ወደ ግብፅ ያመለጡት አይሁዶች ኤርምያስን ይዘውት ሄዱ (ኤር. ፵፫፥፭–፮)፣ በባህል መሰረትም በእዚያ ወግረው ገደሉት።
መፅሐፈ ኤርምያስ
ምዕራፍ ፩–፮ በኢዮስያስ ዘመነ መንግስት የሰጣቸው ትንቢቶችን የያዙ ናቸው። ምዕራፍ ፯–፳ የኢዮአቄም ዘመን ትንቢቶች ነበሩ። ምዕራፍ ፳፩–፴፰ ስለሴዴቅያስ ዘመነ መንግስት ይናገራሉ። ምዕራፍ ፴፱–፵፬ ትንቢቶችን የያዙና ኢየሩሳሌም ከወደቀች በኋላ ስለነበሩት ታሪካዊ ድርጊቶች ይገልጻሉ። ምዕራፍ ፵፭ የጸሀፊው ባሮክ ህይወት እንደሚጠበቅ ለባሮክ የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይይዛል። በመጨረሻም፣ ምዕራፍ ፵፮–፶፩ በውጪ ሀገሮች ላይ የተተነበዩ ትንቢቶች ናቸው። ምዕራፍ ፶፪ የታሪካዊ መጨረሻ ነው። አንዳንዶቹ የኤርምያስ ትንቢቶች ኔፊ ከላባን ባገኘውን በነሀስ ሰሌዳ ውስጥ ነበሩ (፩ ኔፊ ፭፥፲–፲፫)። ኤርምያስም በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል (፩ ኔፊ ፯፥፲፬፤ ሔለ. ፰፥፳)።
መፅሐፈ ኤርምያስ ደግሞም የሰውን ቅድመ ምድራዊ ህይወት እንዳለ ይቀበላል እና ስለኤርምያስ ቀድሞ መመረጥ ይናገራል (ኤር. ፩፥፬–፭)፤ እስራኤል ከመበተናቸው ስለመመለስ፣ አንደኛ ስለከተማና ሁለተኛ ስለቤተሰቡ፣ እስራኤልና ይሁዳ በደህንነት እና በሰላም ለመኖር በሚችሉበት አስደሳች መሬት ወደሆነችው ወደፅዮን የመሰብሰብ ትንቢትን የያዘ (ኤር. ፫፥፲፪–፲፱)፤ እናም ብዙ “ዓሣ አጥማጆች” እና “አዳኞች” በመላክ ጌታ እስራኤልን ከሰሜን ሀገሮች የመሰብሰቡ ትንቢትን የያዘ ነው (ኤር. ፲፮፥፲፬–፳፩)። ይህ የኋለኛው ቀን ድርጊት ሙሴ እስራኤልን ከግብፅ ካወጣበት በላይ ታላቅ የሆነ ድርጊት ይሆናል (ኤር. ፲፮፥፲፫–፲፭፤ ፳፫፥፰)።