አንድ ሺህ አመት ደግሞም ሲዖል; የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ተመልከቱ ክርስቶስ በምድር ላይ ለመንገስ በሚመጣበት ጊዜ የሚጀምረው የ አንድ ሺህ አመት ጊዜ (እ.አ. ፩፥፲)። ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም, ኢሳ. ፪፥፬ (ሚክ. ፬፥፫; ፪ ኔፊ ፲፪፥፬). ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች, ሕዝ. ፴፮፥፴፭. ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ, ራዕ. ፳፥፬. በህዝቦቹ ፅድቅ ምክንያት ሰይጣን ኃይል የለውም, ፩ ኔፊ ፳፪፥፳፮. በጽድቅም ከሰዎች ጋር በምድር ላይ ለአንድ ሺ አመታት እኖራለሁ, ት. እና ቃ. ፳፱፥፲፩. አንድ ሺ አመት ሲጠናቀቅ፣ መሬትን የምተዋት ለትንሽ ጊዜ ይሆናል, ት. እና ቃ. ፳፱፥፳፪. ታላቁ አንድ ሺህ ዘመን ይመጣል, ት. እና ቃ. ፵፫፥፴. ልጆችም ወደ ደህንነት ያለሀጢያት ያድጋሉ, ት. እና ቃ. ፵፭፥፶፰. ልጆች እድሜአቸው እስኪገፋ ድረስም ያድጋሉ፤ ሽማግሌዎችም በቅጽበት ዓይንም ይቀየራሉ, ት. እና ቃ. ፷፫፥፶፩. በሰባት ሺ አመቶች መጀመሪያ ላይ ጌታ አምላክ ምድርን ይቀድሳል, ት. እና ቃ. ፸፯፥፲፪. ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፣ በሕይወት አይኖሩም, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፩. ሰይጣንም ለአንድ ሺህ ለሚሆን ዘመንም አይፈታም, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፲. አንድ ሺህ አመት በግልፅ ተዘርዝሯል, ት. እና ቃ. ፻፩፥፳፫–፴፬. ለአንድ ሺ አመቶችም ምድር ታርፋለች, ሙሴ ፯፥፷፬.