በኩራት ደግሞም መስዋዕት; ምፅዋት፣ የምፅዋት ስጦታ; በጎ ድርገት; አስራት፣ አስራት መክፈል; ጾም፣ መጾም ተመልከቱ ለጌታ የተሰጠ ስጦታ። ብሉይ ኪዳን በብዙ ጊዜ ይህን ቃል መስዋዕቶችን ወይም የሚቃጠሉ በኩራቶችን ለመጠቆም ይጠቀሙባቸዋል። ዛሬ ቤተክርስቲያኗ የጾም በኩራትን እና ሌሎች በነጻ ምርጫ የሚሰጡ በኩራትን (በተጨማሪም ጊዜን፣ ችሎታን፣ እና ንብረቶችን) ደሀን እና ሌሎች ብቁ ምክንያቶችን ለመርዳት ትጠቀምባቸዋለች። በአሥራትና በበኵራት ሰርቃችሁኛል, ሚል. ፫፥፰–፲. አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ, ማቴ. ፭፥፳፫–፳፬. መላ ነፍሳችሁን ለእርሱ እንደ መስዋዕትነት አቅርቡ, ኦምኒ ፩፥፳፮. ሰው ስጦታን ቢያቀርብ ከእውነተኛ ፍላጎት ካልሆነ በቀር ምንም አይጠቅመውም, ሞሮኒ ፯፥፮. የሌዊ ልጆች እንደገና መሰዋዕት ለጌታ በጽድቅ እስኪያቀርቡ ድረስ የአሮናዊ ክህነት ከምድር ላይ ዳግመኛ በፍጹም አይወሰድም, ት. እና ቃ. ፲፫. በዚህ በጌታ ቀን ግን፣ በወንድሞችህ እና በጌታህ ፊት ሀጢያትህን በመናዘዝ፣ መስዋዕትህን እና ቅዱስ ቁርባንህን ለልዑልህ አቅርብ, ት. እና ቃ. ፶፱፥፲፪. እንደ ቤተክርስቲያን እና እንደ ህዝብ ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን እናቅርቡ, ት. እና ቃ. ፻፳፰፥፳፬.