የሰለስቲያል ክብር ደግሞም ከፍተኛነት; የክብር ደረጃዎች; የዘለዓለም ህይወት ተመልከቱ ሰው ከእዚህ ህይወት በኋላ ለማግኘት የሚችለው ከሶስቱ ከፍተኛው የክብር ደረጃ። በእዚህም ጻድቅ የሆነው ከእግዚአብሔር አብ እና ከልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ይኖራል። ደግሞ ሰማያዊ አካል አንድ ነው, ፩ ቆሮ. ፲፭፥፵ (ት. እና ቃ. ፸፮፥፺፮). ጳውሎስ ወደ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ, ፪ ቆሮ. ፲፪፥፪. የሰለስቲያል ክብር በራዕይ ታየ, ት. እና ቃ. ፸፮፥፶–፸. ቅዱሳን በሰለስቲያል አለም ቦታ ከፈለጉ፣ መዘጋጀት አለባቸው, ት. እና ቃ. ፸፰፥፯. በሰለስቲያል መንግስት ህግጋት ለመኖር የማይችል በሰለስቲያል ክብር ለመኖር አይችልም, ት. እና ቃ. ፹፰፥፲፭–፳፪. በሰለስቲያል ክብር ውስጥ ሶስት ሰማያት አሉ፣ ከፍተኛውን የማግኘት ቅድመ ሁኔታ ተዘርዝረዋል, ት. እና ቃ. ፻፴፩፥፩–፪. በተጠያቂነት እድሜዎች ከመድረሳቸው በፊት የሞቱትን ልጆች ሁሉ በሰማይ ሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ይድናሉ, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፲.