ወንጌሎች
የኢየሱስ ምድራዊ ህይወት እና የአገልግሎቱ ድርጊቶች ምስክሮችን የያዙ በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ አራት መፅሐፎች ውስጥ የሚገኙ አራት መዝገቦች። የተጻፉትም በማቴዎስ፣ በማርቆስ፣ በሉቃስ፣ እና በዮሐንስ ነው፣ እነዚህም ስለክርስቶስ ህይወት የተመዘገቡ ምስክሮች ናቸው። በመፅሐፈ ሞርሞን ውስጥ የሚገኘው ፫ ኔፊ መፅሐፍ በብዙ መንገዶች ከእነዚህ አዲስ ኪዳን ወንጌሎች ጋር የተመሳሰለ ነው።
የአዲስ ኪዳን መፅሐፎች በመጀመሪያ የተጻፉት በግሪክ ቋንቋ ነበር። በግሪክ ቋንቋ ወንጌል ማለት “መልካም ዜና” ማለት ነው። መልካሙም ዜና የሰው ዘርን በሙሉ ከሞት ለማዳን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢያት ዋጋ መክፈሉ እና እያንዳንዱን ለስራው ደመወዝ ናቸው። (ዮሐ. ፫፥፲፮፤ ሮሜ ፭፥፲–፲፩፤ ፪ ኔፊ ፱፥፳፮፤ አልማ ፴፬፥፱፤ ት. እና ቃ. ፸፮፥፷፱)
የወንጌሎች ስምምነትን በተጨማሪ መግለጫ ውስጥ ተመልከቱ።