መልከ ጼዴቅ ደግሞም ሳሌም; የመልከ ጼዴቅ ክህነት ተመልከቱ ከጎርፍ በኋላ እና በአብርሐም ዘመን ይኖር የነበረ የብሉይ ኪዳን ታላቅ ሊቀ ካህን፣ ነቢይ እና መሪ። የሳሌም (ኢየሩሳሌም) ንጉስ፣ የሰላም ንጉስ፣ የጻድቅ ንጉስ፣ (ይህም የእብራውያን የመልከ ጼዴቅ ትርጉም ነው)፣ እናም የልዑል እግዚአብሔር ካህን ተብሎ ይጠራ ነበር። አብርሐም ለመልከ ጼዴቅ አስራት ከፈለ, ዘፍጥ. ፲፬፥፲፰–፳. የመልከ ጼዴቅ ህዝቦች ጽድቅን አመጡ፣ እናም ሰማይን አገኙ, ጆ.ስ.ት.፣ ዘፍጥ. ፲፬፥፳፭–፵. ክርስቶስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህን ነበር, ዕብ. ፭፥፮. መልከ ጼዴቅ፣ የሳሌም ንጉስ፣ የልዑል እግዚአብሔር ካህን ነበር, ዕብ. ፯፥፩–፫. ማንም ከመልከ ጼዴቅ በላይ ታላቅ አልነበረም, አልማ ፲፫፥፲፬–፲፱. አብርሐም ክህነትን ከመልከ ጼዴቅ ተቀበለ, ት. እና ቃ. ፹፬፥፲፬. ለጌታ ስም ክብር፣ የጥንት ጊዜ ቤተክርስቲያኗ ክህነትን የመልከ ጼዴቅ ክህነት ብለው ጠሩት, ት. እና ቃ. ፻፯፥፩–፬.