እስማኤል፣ የአብርሐም ልጅ ደግሞም አብርሐም; አጋር ተመልከቱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ የአብርሐምና የሣራ ግብጻዊ ገረድ አጋር ልጅ (ዘፍጥ. ፲፮፥፲፩–፲፮)። ጌታ ለአብርሐምና ለአጋር እስማኤል የታላቅ ሀገሮች አባት እንደሚሆን ቃል ገባላቸው (ዘፍጥ. ፳፩፥፰–፳፩)። ቃል ኪዳኑ የመጣው በእስማኤል ሳይሆን በይስሐቅ ነው, ዘፍጥ. ፲፯፥፲፱–፳፩ (ገላ. ፬፥፳፪–፭፥፩). እግዚአብሔር ፍሬያማ እንዲሆን እስማኤልን ባረከው, ዘፍጥ. ፲፯፥፳. እስማኤል አብርሐምን ለመቅበር ረዳ, ዘፍጥ. ፳፭፥፰–፱. የእስማኤል አስራ ሁለት ወንድ ልጆች ስም ተሰጥተዋል, ዘፍጥ. ፳፭፥፲፪–፲፮. እስማኤል ሞተ, ዘፍጥ. ፳፭፥፲፯–፲፰. ዔሳው የእስማኤል ሴት ልጅ ማዕሌትን ሚስት ትሆነው ዘንድ አገባ, ዘፍጥ. ፳፰፥፱.