ቋንቋ መረጃዎችን፣ ሀሳቦችን፣ እና አስተያየቶችን ለማስተላለፍ በልዩ ንድፎች የሚቀናጁ የተጻፉ ወይም የሚናገሯቸው ቃላቶች። ቋንቋን የምንጠቀምበት መንገድ ስለእግዚአብሔርና ስለሌሎች ሰዎች ያለንን ስሜት ያሳያል። በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ጊዜ ጌታ ለሰው ዘር በሙሉ ንጹህ ቋንቋ ይሰጣል (ሶፎ. ፫፥፰–፱)። ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች, ዘፍጥ. ፲፩፥፩. ጌታ የምድርን ሁሉ ቋንቋ አምታታ, ዘፍጥ. ፲፩፥፬–፱. እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር, የሐዋ. ፪፥፩–፮. ጌታ ለሰዎችም በሚረዱት፣ እንደ ቋንቋቸው ይናገራቸዋል, ፪ ኔፊ ፴፩፥፫ (ት. እና ቃ. ፩፥፳፬). አስተዋይ ሰዎች ይሆኑ ዘንድ፣ በአባቶቻቸው ቋንቋ ሁሉ እንዲማሩ አደረገ, ሞዛያ ፩፥፪–፭. መንፈሱ ትሁት፣ ቋንቋውም ቅንና የሚታነፅ የሆነው፣ የሚናገረውም፣ ስነስርዓቶቼን ካከበረ፣ ይህም ከእግዚአብሔር ነው, ት. እና ቃ. ፶፪፥፲፮. ሁሉንም ቋንቋዎች፣ ልሳኖች፣ እና ህዝቦች እወቁ, ት. እና ቃ. ፺፥፲፭. አዳምና ልጆቹ ንፁህና ያልተበላሸ ቋንቋ ስለነበራቸው, ሙሴ ፮፥፭–፮፣ ፵፮. እግዚአብሔር ለሔኖክ በጣም ሀይለኛ ቋንቋ ሰጠው, ሙሴ ፯፥፲፫.