አዳም
በምድር ላይ የተፈጠረ የመጀመሪያ ሰው።
አዳም የምድር ሰው ዘር አባት እና የአባቶች አለቃ ነው። በዔድን ገነት ውስጥ የተላለፈው (ዘፍጥ. ፫፤ ት. እና ቃ. ፳፱፥፵–፵፪፤ ሙሴ ፬) “እንዲወድቅ” እና ሟች ሆነ፣ ይህም የሰው ዘር በዚህ ምድር ላይ እድገት እንዲኖራቸው አስፈላጊ የሆነ ደረጃ ነበር (፪ ኔፊ ፪፥፲፬–፳፱፤ አልማ ፲፪፥፳፩–፳፮)። ስለዚህ አዳም እና ሔዋን የዘለአለማዊ እድገት እንዲኖረን ስላስቻሉን ለስራ ክፍላቸው መከበር ይገባቸዋል። አዳም በዘመናት የሸመገለውም እና ሚካኤል ተብሎ የሚታወቀው ነው (ዳን. ፯፤ ት. እና ቃ. ፳፯፥፲፩፤ ፻፯፥፶፫–፶፬፤ ፻፲፮፤ ፻፴፰፥፴፰)። እርሱም የመላእክት አለቃ ነው (ት. እና ቃ. ፻፯፥፶፬) እና እንደ ሰው ቤተሰብ የአባቶች አለቃ፣ ለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ዝግጅት እንደገና ወደ ምድር ይመጣል (ት. እና ቃ. ፻፲፮)።