ክፍል ፻፲፮
በግንቦት ፲፱፣ ፲፰፻፴፰ (እ.አ.አ.) በስፕሪንግ ሂል፣ በዴቪስ የግዛት ክፍል፣ ሚዙሪ ውስጥ በራይት ማመላለሻ ጀልባ አጠገብ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ የተሰጠ ራዕይ።
፩ ስፕሪንግ ሂል በጌታ እንደ አዳም-ኦንዳይ-አማን ተጠርቷል፣ ምክንያቱም፣ እንዲህም ይላል፣ ይህም አዳም ህዝቡን ለመጎብኘት የሚመጣበት ወይም፣ በነቢዩ ዳንኤል እንደተነገረው፣ በዘመናት የሸመገለውም የሚቀመጥበት ስፍራ ነው።