፩ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፥ አገልጋዬ ዴቭድ ደብሊው ፓትን በሚመጣው ጸደይ ከሌሎች ጋር፣ እንዲሁም እርሱን ጨምሮ አስራ ሁለት ከሆኑት ጋር፣ ስሜን ለመመስከር እና ለአለም ሁሉ የምስራች ለመውሰድ በተልዕኮ ይሰራልኝ ዘንድ፣ ጉዳዮቹን ሁሉ በቶሎ እንዲያከናውንና የሚሸጡ እቃዎቹን ይሸጥ ዘንድ ፍቃዴ ነው።
፪ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላልና፣ ስሜን የሚክዱ በመካከላችሁ እስካሉ ድረስ፣ በእነርሱ ምትክ የሚተከሉና የኤጲስ ቆጶስ አመራሩን የሚቀበሉ ሌሎች ይኖራሉ። አሜን።