ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፵፯


ክፍል ፵፯

በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በመጋቢት ፰፣ ፲፰፻፴፩ (እ.አ.አ.) በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ከዚህ ጊዜ እንደ ነቢዩ ጸሀፊ ያገለግል የነበረው ጆን ዊትመር የታሪክ ምሁር እና መዝጋቢ ሆኖ በመሾም ኦሊቨር ካውደሪን ለመተካት አመንትቶ ነበር። እንዲህም ጻፈ፣ “ላደርገው አልፈልግም ነበር ግን የጌታን ፈቃድ በዚህ ጉዳይ አከብራለሁ፣ እናምእርሱ ከፈለገው፣ በገላጩ ጆሴፍ በኩል ይህን እንደሚገልጽ ፍላጎቴ ነው።” ጆሴፍ ስሚዝ ይህን ራዕይ ከተቀበለ በኋላ፣ ጆን ዊትመር ተቀበለ እናም በተመደበበት ሀላፊነት አገለገለ።

፩–፬፣ ጆን ዊትመር የቤተክርስቲያኗን ታሪክ እንዲጠብቅ እና ለነቢዩ ጸሀፊ እንዲሆን ተመድቧል።

እነሆ፣ በሌላ ኃላፊነት እስኪጠራ ድረስ አጋልጋዬ ጆን ቀጣይነት ያለው ታሪክ እንዲጽፍና እንዲጠብቅ፣ እናም፣ አገልጋዬ ጆሴፍ፣ የሚሰጡህ ን ነገሮች ሁሉ በመጻፍ እንዲረዳህ በእኔ ዘንድ አስፈላጊ ነው።

ደግሞም፣ እውነት እልሀለሁ በሚያስፈልግበት ጊዜ ሁሉ በስብሰባዎች ላይ እንዲሁ መናገር ይችላል።

ደግሞም፣ እልሀለሁ የቤተክርቲያኗን መዝገብ እና ታሪክ በቋሚነት እንዲጠብቅም ይሾም፤ ኦሊቨር ካውድሪ ሌላ ሀላፊነት ተሰጥቶታልና።

ስለዚህ፣ ታማኝ እስከሆነ ድረስ፣ እነዚህን ነገሮች እንዲፅፍ በአፅናኙ ይሰጠዋል። እንዲህም ይሁን። አሜን።