ክፍል ፻፰
በታህሳስ ፳፮፣ ፲፰፻፴፭ (እ.አ.አ.)፣ በከርትላንድ ኦሀዮ ውስጥ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ይህን ክፍል የተሰጠው ከዚህ በፊት እንደ ሰባ የተሾመውና ሀላፊነቱን እንዲያውቅ ራዕይ ለመጠየቅ ወደ ነቢዩ የመጣው ላይመን ሸርመን በጠየቀበት አይነት ነበር።
፩–፫፣ ላይመን ሸርመን ኃጢአቱ ተሰርዮለታል፤ ፬–፭፣ ከቤተክርስቲያኗ መሪ ሽማግሌዎች ጋር አብሮ ይቆጠር፤ ፮–፰፣ ወንጌሉን እንዲሰብክና ወንድሞቹን እንዲያጠናክር ተጠርቷል።
፩ አግልጋዬ ላይመን ጌታ ለአንተ እንዲህ ይሏል፥ በዚህ ማለዳ ከመደብኩት ምክር ትቀበል ዘንድ ወደዚህ በመምጣትህ ምክንያት ኃጢአትህ ተሰርዮልሀል።
፪ ስለዚህ፣ ስለመንፈሳዊ አቋምህ በሚመለከት ነፍስህ ትረፍ እና ድምጼን መቋቋምህንም አቁም።
፫ እና ተነሳ እና የገባሀውንና የምትገባውን ቃል ኪዳንህን ታከብር ዘንድ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተጨማሪ ተጠንቀቅ፣ እና በጣም ታላቅ በሆኑ በረከቶችም ትባረካለህ።
፬ አገልጋዮቼ በክብር ስብሰባ እንዲሰበሰቡ እስኪጠሩ ድረስ በትእግስት ጠብቅ፣ ከዚያም ከመጀመሪያ ሽማግሌዎቼ ጋር ትታወሳለህ፣ እና ከመረጥኳቸው ከሚቀሩት ሽማግሌዎቼ ጋር መብትን በሹመት ትቀበላለህ።
፭ እነሆ፣ በታማኝነት ከቀጠልክ ይህም ለአንተ የአብ ቃል ኪዳን ነው።
፮ እና ከዚያም ጊዜ በኋላ በምልክህ በማንኛውም ስፍራ ወንጌሌን ለመስበክ መብት ይኖርህ ዘንድ በዚያም ቀን ይህ ይሟላልሀል።
፯ ስለዚህ፣ በንግግርህ ሁሉ፣ በጸሎቶችህ ሁሉ፣ በምታበረታታው ሁሉ፣ እና በምታደርገው ሁሉ ወንድሞችህን አጠናክር።
፰ እነሆም እና አስተውል፣ ልባርክህ እና ላድንህ ለዘለአለም ከአንተ ጋር ነኝ። አሜን።