ክፍል ፺፪
በመጋቢት ፲፭፣ ፲፰፻፴፫ (እ.አ.አ.) በከርትላንድ ኦሀዮ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል የተሰጠ ራዕይ። ራዕዩ በቅርብ ለጆሴፍ ስሚዝ እንደ አማካሪ ለተመደበው ለፍረድሪክ ጂ ዊልያምስ በትብብር ድርጅት ውስጥ ስላለው ሀላፊነት መመሪያ የሚሰጥ ነው (ክፍሎች ፸፰ እና ፹፪ ርዕሶችን ተመልከቱ)።
፩–፪፣ ጌታ በትብብር ስርዓት ውስጥ አባል ስለመሆን ትእዛዝ ሰጥቷል።
፩ በእውነት ጌታ እንዲህ ይላል፣ ከዚህ አስቀድሞ በተሰጠው ትእዛዝ አማካይነት ለተደራጀው የትብብር ስርዓት ስለአገልጋዬ ፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ፣ በስርዓቱ እንድትቀበሉት ዘንድ፣ ራዕይ እና ትእዛዝ ሰጥቻችኋለሁ። ለአንዱ የምለው ለሁሉም እንዲሁ እላለሁ።
፪ ደግሞም፣ ለአገልጋዬ ፍረድሪክ ጂ ዊሊያምስ እላለሁ፣ የዚህ ስርዓት ተሳታፊ አባል ሁን፤ እና የበፊቱን ትእዛዛት በማክበር ታማኝ እስከሆንክ ድረስ ለዘለአለም ትባረካለህ። አሜን።