ቅዱሳት መጻህፍት
ትምህርት እና ቃል ኪዳኖች ፹


ክፍል ፹

በመጋቢት ፯፣ ፲፰፻፴፪ (እ.አ.አ.) በሀይረም ኦሀዮ ውስጥ፣ በነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ በኩል ለስቲቨን ቢዩረት የተሰጠ ራዕይ።

፩–፭፣ ስቲቨን ባርነት እና ኢድን ስሚዝ በሚመርጡበት ስፍራ እንዲሰብኩ ተጠርተዋል።

በእውነት ጌታ ለአንተ አገልጋዬ ስቲቨን ባርነት እንዲህ ይላል፥ ሂድ፣ ወደ አለም ሂድ እናም በድምፅህ አካባቢ ለሚመጣው ፍጥረት ሁሉ ወንጌልን ስበክ

እናም የጉዞ ጓደኛ ከፈለግህ፣ አገልጋዬን ኢድን ስሚዝን እሰጥሀለሁ።

ስለዚህ፣ ሂዱ እናም ወንገሌን ስበኩ፣ ወደ ሰሜን ይሁን ወደ ደቡብ፣ ወደምስራቅ ይሁን ወደምእራብ ግድ የለም፣ አትሳሳቱምና።

ስለዚህ፣ የሰማችሁትን ነገሮች አውጁ፣ እናም በእውነት እመኑ፣ እናም እውነት እንደሆነ እወቁ

እነሆ፣ ይህ የጠራችሁ፣ የቤዛችሁ፣ እንዲሁም የእርሱ የኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ነው። አሜን።