ክፍል ፳፬
ሐምሌ ፲፰፻፴ (እ.አ.አ.) በሀርመኒ፣ ፔንስልቫኒያ፣ ለነቢዩ ጆሴፍ ስሚዝ እና ለኦሊቨር ካውድሪ የተሰጠ ራዕይ። ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ ከተደራጀች አራት ወራት ቢያልፉም ስደቱ ጠንክሯል፣ እናም መሪዎች ራሳቸውን ለተወሰነ ጊዜ በመሰወር ደህንነትን መሻት ነበረባቸው። የሚቀጥሉት ሶስት ራዕይዎች በዚህ ጊዜ እነርሱን ለማጠንከር፣ ለማበረታታት፣ እና ለማስተማር የተሰጡ ናቸው።
፩–፱፣ ጆሴፍ ስሚዝ ቅዱሳን መጻህፍትን ለመተርጎም፣ ለመስበክ፣ እናም ለማብራራት ተጠርቷል ፲–፲፪፣ ኦሊቨር ካውድሪ ወንጌልን ለመስበክ ተጥርቷል፤ ፲፫–፲፱፣ ተአምራትን፣ እርግማንን፣ የእግርን ትቢያ ማራገፍን፣ ለመንገድ ከረጢት ሳይዙ መሄድን የተመለከተ ህግ ተገልጧል።
፩ እነሆ መፅሐፈ ሞርሞንን ለመጻፍ እናም ወደ አገልግሎቴ ተጠርተህ እናም ተመርጠህ ነበር፤ እናም ከስቃይህ ውስጥ ከፍ አድርጌሀለሁ፣ እናም መክሬሀለሁ፣ ከተጠላቶችህም ሁሉ ድነሀል እናም ከሰይጣን እና ከጨለማ ሀይል ታድጌሀለሁ!
፪ ሆኖም፣ በመተላልፍህ ይቅርታን አታገኝም፤ ሆኖም፣ ሂድ ከእንግዲህ ግን ኃጢአትን አትስራ።
፫ ተግባርህን አጉላ፤ እናም በምድርህ ከዘራህ እና ዋስትናውን ካስጠበቅህ በኋላ በኮለስቪል፣ ፈየቴ፣ እናም ማንችስተር ወደሚገኙት ቤተክርስቲያኖች በፍጥነት ሂድ፣ እና እነርሱም ይደግፉሀል፤ እናም በጊዜያዊም ሆነ በመንፈሳዊ በረከት እባርካቸዋለሁ፣
፬ ነገር ግን አንተን የማይቀበሉ ከሆነ፣ በበረከት ፈንታ እርግማንን እልክባቸዋለሁ።
፭ እናም ወደ እግዚአብሔር በስሜ መጣራትን፣ እናም በአጽናኙ የሚሰጡህን ነገሮች መጻፍን፣ እናም ለቤተክርስቲያኗ ቅድሷን መጻህፍትን ሁሉ ማብራራትህን ትቀጥላለህ።
፮ እናም በዚያኑ ጊዜ የምትናገረውን እና የምትጽፈው ይሰጥሀል፣ እናም ይሰሙታል፣ ወይም ከበረከት ይልቅ እርግማንን እልክባቸዋለሁ።
፯ በፅዮን ውስጥ አገልግሎትህን ሁሉ ታደርጋለህና፤ እና በዚህም ጥንካሬን ታገኛለህ።
፰ በስቃይህ ታጋሽ ሁን፣ ብዙም ያጋጥምሀልና፣ ነገር ግን በጽናት አሳልፋቸው፣ እነሆም እስከመጨረሻዎቹ ቀኖችህም እንኳን እኔ ከአንተ ጋር ነኝ።
፱ ይህ የተጠራህበት ስላልሆነ፣ በጊዜያዊ ስራዎች ጥንካሬ አይኖርህም። ለጥሪህ ትኩረትን ስጥ እናም ተግባርህን የምታጎላበትንም፣ እናም ሁሉን ቅዱሳን መጻህፍት የምታብራራበት እናም እጅን መጫንን እና ቤተክርስቲያናቱን የምታጸናበት ሁኔታ ይኖርሀል።
፲ እናም ወንድምህ ኦሊቨር በአለም ፊት እንዲሁ በቤተክርስቲያኗ ስሜን መሸከምን ይቀጥላል። ስለእኔ በቂ ነገርን መናገር እችላለው ብሎ አያስብ፤ እናም፣ አስተውል፣ እኔ እስከመጨረሻው ድረስ ከእርሱ ጋር ነኝ።
፲፩ በድካም ሆነ፣ ወይም በብርታት፣ በእስራትም ሆነ በነጻነት በራሱ ሳይሆን፣ በእኔ ክብረን ያገኛል።
፲፪ እናም በሁሉም ጊዜያት እና በሁሉም ስፍራዎች አፉን ይከፍታል እናም እንደመለከት ድምጽ በቀንና በማታ ወንጌሌን ያውጃል። እናም በሰዎች መካከል የማይታወቅን አይነት ብርታት እሰጠዋለሁ።
፲፫ ዲያብሎስን ከማስወጣት፣ የታመሙትን ከመፈወስ እናም መርዛምን እፉኝት፣ እናም ገዳይን መርዝ ከመቋቋውም በስተቀር እኔ ካላዘዝኳችሁ ሌሎች ተአምራትን አትሹ፤
፲፬ እናም፣ ቅዱሳን መጻህፍት ይፈጸሙ ዘንድ፣ እነዚህን ነገሮች የሚፈልጓቸው ካልጠየቁህ በስተቅር አታደርጋቸውም፣ በተጻፈው መሰረት ታደርጋው ዘንድ ነውና።
፲፭ እናም በምትገቡበት ስፍራ ሁሉ በስሜ ካልተቀበሏችሁ፣ በበረከት ፈንታ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ የእግራችሁን ትቢያ በማራገፍ እናም በመንግድ ዳር ላይ እግራችሁን በማጽዳት እርግማንን ትተዋላችሁ።
፲፮ እናም በአመጽም በእናንተ ላይ እጁን የሚያነሳ ሁሉ በስሜ ይመታ ዘንድ ታዛላችሁ፤ እናም እነሆ፣ እንደ ቃላቶቻችሁ በጊዜዬ እመታቸዋለሁ።
፲፯ እናም ከእናንተ ጋርም ወደ ህግ የሚሄዱትም በህጉ ይረገማሉ።
፲፰ ምንም አይነት ኮረጆም፣ ከረጢትም፣ በትርም ሆነ ሁለት እጅ ጠባብን አትውሰድ፣ ለምግብ፣ ለምትለብሰው፣ እናም ለመጫሚያ እናም ለገንዝብ እናም ለከረጢት የሚያስፈልግህን በዚያው ሰዓት ቤተክርስቲያኗ ትሰጥሀለችና።
፲፱ ስለሆነ በሀያል ግርዘት አዎን ለመጨረሻ ጊዜ፤ የወይን ስፍራዬን እንድትገርዝ ተጠርተሀል፤ እናም የሾምካቸውም ሁሉ በዚህ መንገድ እንዲሁ ያደርጋሉ። አሜን።