ለታመሙት አገልግሎት መስጠት ደግሞም መቀባት; መፈወስ፣ ፈውሶች; እጅን መጫን; ክህነት; ዘይት ተመልከቱ የተቀደሰ ዘይት በመጠቀም፣ የመልከ ጼዴቅ ክህነት ያላቸው ወንዶዎች ለታመሙት የሚሰጡት በረከት። እጅህን ጫንባት, ማቴ. ፱፥፲፰. ኢየሱስ በጥቂቶች ድውዮች ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው, ማር. ፮፥፭. የክርስቶስ ሀዋሪያት ብዙ ድውዮችንም ዘይት እየቀቡ ፈወሱአቸው, ማር. ፮፥፲፫. ሽማግሌዎች ድውዮችንም ዘይት ቀብተው ይፈውሳሉ, ያዕ. ፭፥፲፬–፲፭. ይህን የሚፈልጉት ካልጠየቁህ በስተቅር፣ የታመሙትን አትፈውስ, ት. እና ቃ. ፳፬፥፲፫–፲፬. ሽማግሌዎች በታመሙት ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ, ት. እና ቃ. ፵፪፥፵፬. በታመሙትም ላይ እጆችህን ጫን፣ እናም ይድናሉ, ት. እና ቃ. ፷፮፥፱.