የቅዱሳት መጻህፍት መመሪያ በመፅሐፍ ቅዱስ፣ በመፅሐፈ ሞርሞን፣ በትምህርት እና ቃል ኪዳኖች፣ እና በታላቅ ዋጋ ዕንቁ ውስጥ የሚገኙትን የተመረጡ ትምህርቶችን፣ መሰረታዊ መመሪያዎችን፣ ሰዎች፣ እና ቦታዎችን የሚያብራራ ነው። ይህም ለእያንዳንዱ ርዕስ ጥናታችሁ ዋና የቅዱሳት መጻህፍት ማጣቀሻ ያቀርብላችኋል። ይህ መመሪያ በግል እና በቤተሰባችሁ የቅዱሳት መጻህፍት ጥናት ሊረዳችሁ ይችላል። ስለወንጌል ያላችሁን ጥያቄ ለመመለስ፣ ለቅዱሳት መጻህፍት ርዕሶች ጥናት፣ ንግግሮች እና ትምህርቶችን ለማዘጋጀት፣ እና ስለወንጌል ያላችሁን እውቀት እና ምስክር ለማሳደግ ይረዳችኋል።