አለት ደግሞም ራዕይ; ኢየሱስ ክርስቶስ; ወንጌል ተመልከቱ በምሳሌ፣ ጠንካራ መሰረት እና መደገፊያ የሆኑት ኢየሱስ ክርስቶስ እና ወንጌሉ (ት. እና ቃ. ፲፩፥፳፬፤ ፴፫፥፲፪–፲፫)። አለት ደግሞም እግዚአብሔር ወንጌሉን ለሰው የሚያሳውቅበት ራዕይ መሆንም ይችላል (ማቴ. ፲፮፥፲፭–፲፰)። እርሱ አምላክ ነው፤ ሥራውም ፍጹም ነው, ዘዳግ. ፴፪፥፬. እግዚአብሔር ዓለቴ ነው፤ በእርሱም እታመናለሁ, ፪ ሳሙ. ፳፪፥፪–፫. እጅም ሳይነካው ድንጋይ ከተራራው ተፈነቀለ, ዳን. ፪፥፴፬–፴፭. በዓለት ላይም ተመስርቷል, ማቴ. ፯፥፳፭ (፫ ኔፊ ፲፬፥፳፭). ኢየሱስ ክርስቶስ የተናቀው ድንጋይ ነው, የሐዋ. ፬፥፲–፲፩. ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ, ፩ ቆሮ. ፲፥፩–፬ (ዘፀአ. ፲፯፥፮). በአለት ላይ የሰራ እውነትን ይቀበላል, ፪ ኔፊ ፳፰፥፳፰. አይሁዶች የሚገነቡበት አለት [ክርስቶስን] አይቀበሉም, ያዕቆ. ፬፥፲፭–፲፯. በቤዛነት ዓለታችን ላይ ነው መሰረታችንን መገንባት ያለብን, ሔለ. ፭፥፲፪. በክርስቶስ ትምህርት የሚገነባ በአለቱ ላይ ይገነባል እናም የጥፋት ውሀው ሲመጣ አይወድቅም, ፫ ኔፊ ፲፩፥፴፱–፵ (ማቴ. ፯፥፳፬–፳፯; ፫ ኔፊ ፲፰፥፲፪–፲፫). ጠቢብ ሰው ቤቱን በአለት ላይ ሰራ, ፫ ኔፊ ፲፬፥፳፬. በእኔ ዐለት ላይ ከተገነባችሁ ሊቋቋሟችሁ አይችሉም, ት. እና ቃ. ፮፥፴፬. በዚህ አለት ላይ የተመሰረተም አይወድቅም, ት. እና ቃ. ፶፥፵፬. እኔ የፅዮን ንጉስ፣ የሰማይ ዓለት፣ መሲሕ ነኝ, ሙሴ ፯፥፶፫.