ዔድን
የመጀመሪያ ወላጆቻችን፣ አዳምና ሔዋን፣ ቤት (ዘፍጥ. ፪፥፰–፫፥፳፬፤ ፬፥፲፮፤ ፪ ኔፊ ፪፥፲፱–፳፭፤ ሙሴ ፫–፬፤ አብር. ፭)፣ ይህም በስተምስራቅ ዔድን እንደገነት ተመድቦ ነበር። አዳምና ሔዋን የተከለከለውን ፍሬ ከበሉ በኋላና ሟች ከሆኑ በኋላ ከዔድን እንዲወጡ ተደረጉ (ሙሴ ፬፥፳፱)። የኋለኛው ቀን ራዕይ የመፅሐፍ ቅዱስ የዔድን ገነት ታሪክን አረጋግጧል። ገነት ይገኝበት የነበረው አሁን የሰሜን አሜሪካ በሚባለው ክፍለ አህጉር ውስጥ እንደነበረ አስፈላጊ መረጃ ጨምሯል።