የጥናት እርዳታዎች
ደም


ደም

በጥንት እስራኤላውያን እና ዛሬም በብዙ ባህሎች እንደ ህይወት መቀመጫ ወይም የስጋ በሙሉ በጣም አስፈላጊ ሀይል እንደሆነ ይታያል። በብሉይ ኪዳን ጊዜዎች ውስጥ ጌታ እስራኤላውያንን ደምን እንደምግብ እንዳይበሉ ከለከላቸው (ዘሌዋ. ፫፥፲፯፯፥፳፮–፳፯፲፯፥፲–፲፬)።

የመስዋዕት የኃጢያት ዋጋ መክፈያ ሀይል ያለው በደም ውስጥ ነበር ምክንያቱም ደም ለህይወት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ስለሚታሰብበታል። በብሉይ ኪዳን ውስጥ የነበረው የእንስሳት መስዋዕት በኋላ ኢየሱስ የሚፈፅመው ታላቅ መስዋዕት ምስሌ ነበር (ዘሌዋ. ፲፯፥፲፩ሙሴ ፭፥፭–፯)። የኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢያት ክፍያ ደም ንስሀ የሚገባውን ያጸዳል (፩ ዮሐ. ፩፥፯)።