ጨው በጥንት አለም ውስጥ የሚጠቀሙበት ምግብን ለረጅም ጊዜ ማቆያ፤ ይህም ለህይወት አስፈላጊ እንደሆነ ይታይ ነበር። የሎጥም ሚስት የጨው ሐውልትም ሆነች, ዘፍጥ. ፲፱፥፳፮. እናንተ የምድር ጨው ናችሁ, ማቴ. ፭፥፲፫ (ሉቃ. ፲፬፥፴፬; ፫ ኔፊ ፲፪፥፲፫). የጌታ የቃል ኪዳን ህዝቦች እንደምድር ጨው ሆነው ይቆጠራሉ, ት. እና ቃ. ፻፩፥፴፱–፵. ቅዱሳን የሰዎች አዳኞች እስካልሆኑ ድረስ፣ ጣዕሙን እንዳጣ ጨው ይሆናሉ, ት. እና ቃ. ፻፫፥፱–፲.