መዝሙር ደግሞም መዘመር; ሙዚቃ ተመልከቱ እግዚአብሔር የሚሞገስበት መዝሙር። ጌታ ወደ ጌቴሴማኒ ከመሄዱ በፊት አስራ ሁለቱ ሐዋሪያት መዝሙር ዘመሩ, ማቴ. ፳፮፥፴. ጌታ ኤማ ስሚዝ ቅዱስ መዝሙሮችን ለመምረጥ አዘዛት, ት. እና ቃ. ፳፭፥፲፩. የጻድቅን መዝሙር ለእኔ ጸሎት ነው፣ በረከት በራሳቸው ላይ በማድረግ ይመለስላቸዋል, ት. እና ቃ. ፳፭፥፲፪. ጌታን በመዝሙርና በሙዚቃ አምልኩ, ት. እና ቃ. ፻፴፮፥፳፰.