ደህንነት ደግሞም መንፈሳዊ ሞት; ስጋዊ ሞት; ቤዛ፣ ማዳን፣ ቤዛነት; ኢየሱስ ክርስቶስ; ከፍተኛነት; የኃጢያት ዋጋን መክፈል፣ የኃጢያት ክፍያ; የቤዛነት ዕቅድ; ጸጋ ተመልከቱ ከስጋዊ እና መንፈሳዊ ሞት መዳን። ሁሉም ሰዎች ከስጋዊ ሞት በእግዚአብሔር ጸጋ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ በኩል፣ ይድናሉ። ደግሞም እያንዳንዱ ግለሰብ ከመንፈስ ሞት በኢየሱስ ክርስቶ በማመን፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ለመዳንም ይችላሉ። ይህም እምነት የሚገለጸው በህግጋትና በወንጌል ስነስርዓቶች ታዛዥ በሆነ ህይወት እና ክርስቶስን በማገልገል ነው። እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው, መዝ. ፳፯፥፩. እርሱ አምላኬ መድኃኒቴም ነው, መዝ. ፷፪፥፪. በወንጌል የሚያድን የእግዚአብሔር ኃይል ነው, ሮሜ ፩፥፲፮ (ት. እና ቃ. ፷፰፥፬). የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ, ፊልጵ. ፪፥፲፪. እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ ለመዳን መርጦአችኋል, ፪ ተሰ. ፪፥፲፫. ደህንነትም ነፃ ነው, ፪ ኔፊ ፪፥፬. ከደህንነት በላይ የሆነ ምንም ስጦታ የለም, ት. እና ቃ. ፮፥፲፫. ደህንነት ለመምጣት የሚያስችለው የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው, ሙሴ ፮፥፶፪ (የሐዋ. ፬፥፲–፲፪). የሰው ዘሮች ሁሉ በክርስቶስ ኃጢያት ክፍያ በኩል መዳን እንደሚችሉ እናምናለን, እ.አ. ፩፥፫. የልጆች ደህንነት እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም, ማቴ. ፲፰፥፫. ትናንሽ ልጆች ዘለዓለማዊ ህይወት ይኖራቸዋል, ሞዛያ ፲፭፥፳፭. የህጻን ጥምቀት እርኩሰት ነው፣ እናም ትንሽ ልጆች በኃጢያት ክፍያ ምክንያት በክርስቶስ ህያው ናቸው, ሞሮኒ ፰፥፰–፳፬. ህጻናት ከአለም መጀመሪያ ጀምሮ በአንድያ ልጄ ድነዋል፤ ለመፈተን ሰይጣን ሃይል አልተሰጠውም, ት. እና ቃ. ፳፱፥፵፮–፵፯. ልጆች ወንጌልን ይማሩ እና በስምንት አመታቸው ይጠመቁ, ት. እና ቃ. ፷፰፥፳፭–፳፰. በኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢያት ክፍያ በኩል ትንሽ ልጆች የተቀደሱ ናቸው, ት. እና ቃ. ፸፬፥፯. ሰዎችም እንደገና በህጻንነት በእግዚአብሔር ፊት የዋህ ሆኑ, ት. እና ቃ. ፺፫፥፴፰. በተጠያቂነት እድሜዎች ከመድረሳቸው በፊት የሞቱትን ልጆች ሁሉ በሰለስቲያል መንግስት ውስጥ ድነዋል, ት. እና ቃ. ፻፴፯፥፲. ልጆች ከአለም መሰረት ጊዜ ጀምሮ ከኅጥያት ንጹህ ናቸው, ሙሴ ፮፥፶፬.