ስጋዊ ደግሞም ስሜታዊ፣ ስሜታዊነት; የአዳም እና የሔዋን ውድቀት; ፍጥረታዊ ሰው ተመልከቱ መንፈሳዊ ያልሆኑ አንዳንድ ነገሮች፣ በልዩም ይህ ቃል ስጋዊ ወይም ጊዜአዊ (ት. እና ቃ. ፷፯፥፲) ወይም አለማዊ፣ ስጋዊ፣ እና ስሜታዊ ለማለት ይጠቀምበታል (ሞዛያ ፲፮፥፲–፲፪)። ስለዓለም ማሰብ ሞት ነው, ፪ ኔፊ ፱፥፴፱. ዲያብሎስ ቀስ ብሎም ወደ ስጋዊ ደህንነት ያባብላቸዋል, ፪ ኔፊ ፳፰፥፳፩. እራሳቸውን በስጋቸው ሁኔታ ተመለከቱ, ሞዛያ ፬፥፪. በስጋዊ ተፈጥሮው የቆየ ወድቆ ይቀራል, ሞዛያ ፲፮፥፭. ሁሉም ከእግዚአብሔር በመወለድ፣ ከስጋዊና ከወደቁበት ሁኔታ ይቀየራሉ, ሞዛያ ፳፯፥፳፭. ሰዎች ስጋዊ፣ ስሜታዊ፣ እናም ዲያብሎሳዊ ናቸው, አልማ ፵፪፥፲. ስጋን እና የራሱን ፍቃድ የሚከተለው መውደቅ አለበት, ት. እና ቃ. ፫፥፬. ሰው በስጋዊ አዕምሮው እግዚአብሔርን ማየት አይችልም, ት. እና ቃ. ፷፯፥፲–፲፪. ሰዎችም ስጋዊ፣ ስሜታዊና ዲያብሎሳዊ መሆን ጀመሩ, ሙሴ ፭፥፲፫፤ ፮፥፵፱.