ሰላም ደግሞም ሰላም የሚሰራ; አንድ ሺህ አመት; እረፍት ተመልከቱ በቅዱሣት መጻህፍት ውስጥ፣ ሰላም ከጸብ እና ብጥበጣ ነጻ መሆን ወይም ለታማኝ ቅዱሳኑ እግዚአብሔር በሚሰጠ መንፈስ የሚመጡ የውስጥ መረጋጋት እና ምቾት ማለት ነው። ከጥላቻ እና ከብጥበጣ ነጻ መሆን ጦርንም ይቈርጣል, መዝ. ፵፮፥፱. ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም, ኢሳ. ፪፥፬. ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ፤ ራሳችሁ አትበቀሉ, ሮሜ ፲፪፥፲፰–፳፩. በምድሪቱ ሠላም ሰፈነ, ፬ ኔፊ ፩፥፬፣ ፲፭–፳. ጦርነትን አስወግዱና ሰላም አውጁ, ት. እና ቃ. ፺፰፥፲፮. የሰላም ምልክት ያንሱ, ት. እና ቃ. ፻፭፥፴፱. ለታዛዥ ከእግዚአብሔር የሚመጣ ሰላም አዳኝ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል, ኢሳ. ፱፥፮. ለክፉዎች ሰላም የላቸውም, ኢሳ. ፵፰፥፳፪. ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር አሉ, ሉቃ. ፪፥፲፫–፲፬. ሰላምን እተውላችኋለሁ, ዮሐ. ፲፬፥፳፯. የእግዚአብሔር ሰላም አሳባችሁን ይጠብቃል, ፊልጵ. ፬፥፯. የንጉስ ቤንያምህዝብ የህሊና ሰላምን ተቀበሉ, ሞዛያ ፬፥፫. በተራራው ላይ ሰላምን የሚያውጁት እግራቸው እንዴት ያማረ ነው, ሞዛያ ፲፭፥፲፬–፲፰ (ኢሳ. ፶፪፥፯). አልማ ወደ ጌታ ጮኸ እናም ሰላምን አገኛ, አልማ ፴፰፥፰. የፃድቃኖች መንፈስ ወደ ሰላም ቦታ ይገባሉ, አልማ ፵፥፲፪. ይህንን ነገር በተመለከተ በአምሮህ ሰላምን አልተናገርኩም, ት. እና ቃ. ፮፥፳፫. ከእኔ ተማር፣ እናም ቃላቴን አድምጥ፤ በመንፈሴ በትህትና ተጓዝ፣ እናም በእኔ ሰላምን ታገኛለህ, ት. እና ቃ. ፲፱፥፳፫. የጻድቅ ስራ የሚሰራው ሰላም ይቀበላል, ት. እና ቃ. ፶፱፥፳፫. የፍጹምነትና የሰላም ማሰሪያ በሆነው በልግስና ማሰሪያ ራሳችሁን አልብሱ, ት. እና ቃ. ፹፰፥፻፳፭. ልጄ፣ በነፍስህ ሰላም ይኑርህ, ት. እና ቃ. ፻፳፩፥፯. ታላቅ ሰላም እንዳሉም ስላወኩኝ፣ የአባቶችን በረከቶች ለማግኘት ፈለኩኝ, አብር. ፩፥፪.