ፈሪሳዊያን
በአዲስ ኪዳን ውስጥ፣ በአይሁዶች መካከል የሚገኙ ስማቸው መለየትን የሚያመለክት የሀይማኖት ቡድኖች። ፈሪሳዊያን የሙሴን ህግ በጥብቅ በመከተላቸው እና ከአህዛብ ጋር የተገናኙ ነገሮችን በማስወገዳቸው ኩራት ነበራቸው። ከሞት በኋላ ህይወት፣ በትንሳኤ፣ እና በመላእክትና በመንፈሶች ህያውነት ያምኑ ነበር። በአፍ የሚተላለፍ ህግ እና በባህል የተጻፉ ህግጋት አስፈላጊ እንደሆኑ ያምናሉ። ሀይማኖትን በሚከተሏቸው ህግ ይቀንሷቸዋል እናም መንፈሳዊ ትዕቢትን ያበረታታሉ። ብዙ የአይሁዳ ህዝብ ክርስቶስን እና ወንጌሉን እንዲጠራጠሩ አደረጉ። ጌታ ፈሪሳዊያንን እና የሚሰሩትን በማቴዎስ ፳፫፤ ማርቆስ ፯፥፩–፳፫፤ እና ሉቃስ ፲፩፥፴፯–፵፬ ውስጥ ወገሰ።